Friday, February 5, 2021

የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች የድጋፍ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ

የጀርመን ቴክኒካ(ል)ዊ ትብብር (Giz/SI jobs) የስልጠናና የስራ ፈጠራ ኘሮጀክት በኢትዮጲያ ስራ ፈጠራን         ለማሳደግ የቢዝነስ ተቋማትን የሚያበረታታ ኘሮጀክት ነዉ።  በዚህም መሰረት ለድጋፍ ከተመረጡ የስራ ዘርፎች አንዱ ግብርና ሲሆን፤ በዚህም ዘርፍ በግብርና ተዋፅኦ ላይ አፅኖት በመስጠት ይሰራል። ለድጋፍ ከተመረጡ መስኮች መካከል በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች በተቀዳሚነት ይሳተፋሉ። በድጋፉ የአስተደዳሪያዊ ስልጠና እዲሁም የማሽነሪ ግዥ ድጋፍ ለ15 /ለአስራ አምስት/ የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች የሚሰጥ ይሆናል። ተጠቃሹ ድጋፍ በዋነኝነት በግብርና መስክ ንቁ ተሳትፎ ያላቸዉን ያቀፈ ይሆናል ። ቀዝቃዛ የአየር ጠባይ ያላቸው አገሮች ቲማቲም የሚያመርቱት በመስተዋት ቤቶች ውስጥ ሲሆን ደረቅ አካባቢዎች ደግሞ ይህን አትክልት የሚያሳድጉት ሃይድሮፖኒክ በሚባል ዘዴ፣ ይኸውም አፈር ሳይኖረው በአፈር ውስጥ የሚገኙት ለተክሉ እድገት የሚያስፈልጉ አልሚ ምግቦች በውኃ ሟምተው በተዘጋጁበት ፈሳሽ ውስጥ ነው።

በድጋፉ በተቀዳሚነት የውኃ በቀል ግብርና (ሃይድሮፖኒክ) ስራን፣ የጓሮ ግብርናን፣ በጣሪያ ላይ የሚደረግ የግብርና ስራን እና የሰፊ እርሻ አስተዳደርን እንዲሁም የመስኖ ስራን ያቀፈ ነዉ። በተጨማሪም የምርት ማቀነባበር ወይም የምርት እሴት ጭማሮን ለአብነት የመጀመሪያ ፣ የሁለተኛና የሦስተኛ ደረጃ እሴት ጭማሮዎችን እና በገበያ ትስስር (ለምሣሌ የምርት ግዥን ፣ የምርት ስም ልዩ መጠሪያንና በስሩ የሚካተቱትን የምርት ዓይነቶች) ላይ ላተኮሩ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ የሚሰጥ ይሆናል።

በአጠቃላይ  የድጋፉ አላማዎች ስራን መፈጠር ሲሆን፤ ዋና አላማዉም አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶችን  አቅም በማዳበር  በተለይም  ድጋፉ  ተጠቃሾቹ   ያላቸዉን   የምርት  ጥራትና  ብዛት  ፣የገበያ ትስስር   እንዲሁም  ዘላቂ  የገንዘብ አቅምን ማዳበር ነዉ። ይህም ከዚህ በታች  በተዘረዘሩት  5 ጠቋሚ መገለጫዎችተመልክቷል።  

  1. የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ የድርጅቶች  ምርት ጥራት ፣ምርታማነት እንዲሁም የገበያ ድርሻ በመጨመር የስራ እድሎች እንዲፈጠሩ ማድረግ። 
  2. የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች ፈጠራ ለመጨመር እንዲሁም ጥናቶችን በማካሄድ የምርት ብሎም የአገልግሎት ብዛት እንዲጎለብት ማድረግ ። 
  3. የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች ያላቸዉን ገበያ በማጠናከር ተጨማሪ የገበያ ትስስሮችን መፈጠር።
  4. ሀገራዊና አለምአቀፋዊ የቴክኖሎጂና የገበያ እንዲሁም ተዛማጅ ትስስሮችን ማጠናከር። 
  5. የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች የገንዘብ አቅም በመጨመር አመርቂ የቢዝነስ አስተዳደር ማስገኘት እንዲሁም መልካም የቢዝነስ ግብይት ስርዓቱን መፍጠር በተጨማሪም የዉጪ የገንዘብ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል ነው። 

ተሳታፊ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶችን ለመሳተፍ መመዘኛዎች 

በአጠቃላይ በድጋፉ መሳተፍ  የሚችሉት የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች ናቸዉ። በተለይም የሚከተሉት የህጋዊ ሰዉነት ሚረጋገጫና  የድርጀት ምዝገባ ዶክመቶች(ሰነዶች ) ማሙዋላት ይኖርባቸዋል ። 

  1. ድርጅቱ ሕጋዊ ሰውነት ሊኖረው ይገባል  
  1. በኢትዮጵያ የተመዘገበ በተሰማራበት ስራ ቢያንስ ለሁለት አመት ያገለገለ 
  1. ባለፈው የአንድ አመት ሽያጭ  1ሚሊየን ወይም ከዚያ በላይ ያገኘ 
  2. አመልካች የግል ድርጅት የሆነና በኢትዮጵያ የንግድ ምዝገባ ሕግ መሰረት የተመዘገበ መሆን ይኖርበታል(መንግሥታዊ ያልሆነ )
  1. ድርጅቱ ሊፈጥር ስለሚችላቸዉ የስራ እድሎች  ገምጋሚ ፅሁፍ ማስገባት ይኖርበታል (ይህም በሚቀጥሉሁለት አመታት በትንሹ ለአስራ አምስት ሰዎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን የሚገልፅ መሆን አለበት 
  1. ድርጅቱ የሚወዳደርበት ፕሮጀክት እራሱ መተግበር አለበት  
  1. ድርጅቱ ቀጣይነት እንዳለውና ስራዉን በቋሚነት ሲሰራ መቆየቱን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ 

ይኖርበታል።  

በአጠቃላይ ድጋፉ እስከ 1,000,000 ብር የሚደርስ ሁኖ የሚከተሉትን አገልግሎትንም ያጠቃልላል።  

  • ስለ ቢዝነስ እቅድ የሚሰጥ የስልጠና ፕሮግራም 

ይህም የእቅድ መንደፍን፣ የሽያጭና ማከፍፈል እቅድን ፣ የሰዉ ሀይል አስተዳደር እቅድን፣ የምርት ብቃት፣ የአቅርቦት ትስስር ጥናት  ስልጠናው በስራ ፈጠራዉ እቅድ የሚዘጋጅና የሚዋቀር ሲሆን ግለሰቦችና ቡድኖች የሚሳተፉበት ይሆናል ። 

  • በአማካሪ የሚሰጥ የሙያ ድጋፍ 

ይህ የምርት ጥራት ማሻሻልን የገበያ እድገትን ወይም በተወዳዳሪዉ ጥያቄ የገንዘብ ምክርን ይጨምራል 

  • የማሽን ግዥ  

የአነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ድጋፉ የማሽን ግዢ ያደርጋል ። ይህም  20%  የማሽን  ክፍያ  በአመልካቾች   የሚፈፀም  ይሆናል።  የማሽኑ  ዋጋ  ከ450,000.00 ብር  መብለጥ  የለበትም። 

  • የማመልከቻ ሂደት 

ፍላጎት ያላቸው ስራ ፈጣሪዎች የምርት  ሀሳባቸውን እንዲሁም ያስፈልጋል የሚሉትን ሰነድ በመግለፅ ለስራ ፈጠራ ድርጅት በአባሪ በተዘጋጀዉ የማመልከቻ  ቅፅ ማቅረብ  ይችላሉ።   ማመልከቻዎቹ  በእንግሊዘኛ  ተፅፈዉ  መቅረብ  ይኖርባቸዋል። 

የድጋፉ ዉጤታማነት እንዲሁም የማሺነሪ  ግዥ   ድጋፉ  ምን  ያህል  የምርት  ማነቆዎችን  መፍታት  ይችላል  የሚለውን  ለማጣራት  የድጋፍ  ዉሳኔው  ከመሰጠቱ  በፊት  በአነስተኛና  መካከለኛ  ድርጅቶች  ላይ  እዉቀት  ያላቸው  ባለሙያዎች  በተመረጡ  ድርጅቶች  ላይ  የጠንካራና  የደካማ  ጎን  ምዘና  እንዲሁም  የአስተዳደር  ብቃት  ምዘና  ያደርጋሉ።  ስለዚህ  በድጋፍ  መካተት  ወይም  አለመካተት  በተሰበሰበው  መረጃ  ላይ መሰረት ያደረገ የሆናል። 

ከማመልከቻ ፎርም በተጨማሪ የሚከተሉት ሰነዶች መቅረብ አለባቸው 

  1. በአባሪ ሐ ላይ እንደሰፈረዉ የአመልካች ሙሉ መረጃ፣ ፌርማ እንዲሁም ስልጣን በተሰጠዉ የድርጅቱ አካል ማህተም መቀመጥ ይኖርበታል
  2. በአባሪ  ላይ እንደሰፈረዉ የህጋዊ አካሉ መለያ 
  3. ለአለፉት አመታት የነበሩ የገቢ መግለጫ እንዲሁም  የገቢ እና ወጪ መመዝገቢያ ሰነድ መቀመጥ ይኖርበታል 

አሸናፊ  ድርጅቶች  የአገልግሎት  የሙያ  የማሽን  ድጋፍ  ከጀርመን  ሙያዊ  ትብብር  ልዩ  የስራ  ፈጠራ  ኢኒሼቲቨ  የሚያገኙ  ይሆናል።  ኘሮጀክቱ  ሊተገበርበት  የተያዘለት  ጊዜ  ስምምነቱ  ከተፈረመበት  ቀን አንስቶ 15 ወራት በማይበልጥ ጊዜ ዉስጥ ይሆናል።  

ማመልከቻ መስገቢያ ዘዴዎች 

የማመልከቻ  ፎርሙ  በኢሜል  ወይም  በሲዲ  እንዲሁም  2 ኮፓ  በህትመት  የቀረቡ  መሆን  አለባቸው  ይህንንም  በተጠቀሰው አድራሻ እስከ የካቲት3/ 2013 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባችዋል:: 

የኢሜል አድራሻ፦ selome.melese@sequa.de 

ሞባይል ቁጥር ፡ 0939-281316 ወይም 0912-403055

የቢሮ አድራሻ ፦ GIZ SI Job መስቀል ፍላወር አስቴር ኘላዛ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ